Prosperity Party

በኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ቦረና ህዝብ እና የቄለም ወለጋ ዞን የሰዲ ጫንቃ ወረዳ ነዋሪዎች ለብልፅግና ፓርቲ ያለውን የማይናወጥ ድጋፍ በታላቅ ሰልፍ አረጋገጡ!

በነገሌ ቦረና ከተማ የሰባተኛው ዙር ብሄራዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ "ምረጡኝ" ቅስቀሳ በታላቅ ህዝባዊ ንቅናቄ ተካሂዷል። በዕለቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጨፌ ኦሮሚያ የመንግስት ተቋማትና ሀብት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ገመቹ አራርሳ፤ ብልፅግና ፓርቲ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሀገርን ከጥፋት የታደገና የህዝብን ትግል ወደ ተጨባጭ ድል የቀየረ የለውጥ ኃይል መሆኑን ገልጸዋል። ፓርቲው ብቃትና የህዝብ ዉግንና ያላቸውን እጩዎች በማቅረብ የተጀመረውን ሁለንተናዊ ብልፅግና ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግር አረጋግጠዋል።

የምስራቅ ቦረና ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱረዛቅ ሁሴን እና የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም አብዲ በበኩላቸው፤ ፓርቲው የአርብቶ አደሩን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑንና ባለፉት አምስት ዓመታት በዞኑ ተስፋ ሰጪ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል። እንዲሁም የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች አደረጃጀት ኃላፊ ወይዘሮ ሳዲያ መሀመድ፤ ፓርቲው ኢትዮጵያን በአፍሪካና በዓለም አደባባይ አርአያ እያደረገ መሆኑን ገልጸው፣ ህዝቡ ድምጹን ለብልፅግና እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

የአካባቢው አርብቶ አደር ማህበረሰብም የመሰረተ ልማት፣ የውሃ እና የእንስሳት ጤና ችግሮቻቸው በብልፅግና መንግስት ልዩ ትኩረት ማግኘታቸውን በመጥቀስ፤ የጀመሩትን የብልፅግና ጉዞ ለማስቀጠል በምርጫው የስንዴ ነዶን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን በደማቅ ሰልፍ አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል በቄለም ወለጋ ዞን የሰዲ ጫንቃ ወረዳ ነዋሪዎች በታላቅ የድጋፍ ሰልፍ ለብልጽግና ፓርቲ ያላቸውን ጽኑ ድጋፍ በተግባር አሳይተዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎችን ያሳተፈው ይሄው የ"ምረጡኝ" ቅስቀሳ መርሃ ግብር፣ በወረዳው የተመዘገቡ የልማት ስኬቶችን በማብሰር እና የነገዋን ኢትዮጵያ ተስፋ በማድመቅ በልዩ ድምቀት ተካሂዷል። ሰልፈኞቹ የብልጽግና ጉዞ የጀመረውን ሁለንተናዊ ለውጥ በማድነቅ፣ በተለይም በግብርናው ዘርፍ የታየውን ስንዴ ምርታማነት እና የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎችን እንደ ትልቅ ስኬት አንስተዋል።

የሰዲ ጫንቃ ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ "ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥና የጀመርነውን የብልጽግና ጉዞ ዳር ለማድረስ ምርጫችን ብልጽግና ነው" ሲሉ በታላቅ መነሳሳት አረጋግጠዋል። ፓርቲው ባለፉት ዓመታት የገጠሩን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ያደረጉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በማከናወን፣ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የገባውን ቃል በተግባር እያሳየ ይገኛል። ይህ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍም ፓርቲው ለህዝብ ጥያቄዎች የሚሰጠው ምላሽ እና የጀመረው የለውጥ ጉዞ በህዝብ ዘንድ ያለውን ከፍተኛ ተቀባይነት የሚያሳይ ነው።

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
ምርጫችን ለብልፅግና!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!

#prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party