በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ንቅናቄ በታላቅ ድምቀት እየተካሄደ ነዉ
በአፋር ክልል የብልፅግና ፓርቲን ዓላማና የሪፎርም ጉዞዎችን ለመደገፍ የተዘጋጀ ታላቅ የሕዝብ ድጋፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ ንቅናቄ እየተካሄደ ይገኛል።
በክልሉ ዋና ከተማ ሰመራ እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና የሴቶች አደረጃጀቶች በሰልፉ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። ሰልፈኞቹ የክልሉን ሁለንተናዊ ልማት፣ በተለይም በቆላማ አካባቢዎች የተመዘገቡ የየብስ ስንዴ ልማትና የመስኖ መሠረተ ልማት ስኬቶችን የሚያደንቁ መፈክሮችን እያስተጋቡ ነው።
በተጨማሪም በክልሉ እየታየ ያለውን አንጻራዊ ሰላምና የአብሮነት እሴት አጠናክሮ ለማስቀጠል ከመንግሥት ጎን እንደሚቆሙ ሰልፈኞቹ በቁርጠኝነት እየገለጹ ይገኛሉ። በሰልፉ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተው መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
#prosperity