Prosperity Party

በአርባ ምንጭ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ

በአርባ ምንጭ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

የብልጽግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐ-ግብር “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሐሳብ በአርባምንጭ ከተማ በደማቅ ሁነታ እየተካሄደ ይገኛል። 

ፓርቲው በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ባለፉት አምስት ዓመታት ሰፊ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል። በሚቀጥሉት አምስት ዓመታትም አስተማማኝና ተቋማዊ መሰረት ያለው የፖለቲካ ባህል በመገንባት፤ ዘላቂ ሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ ብሔራዊ መግባባት፣ የዜጎች ክብር፣ ፍትሃዊነት እና የጋራ ብልፅግና የተረጋገጠባትን ሀገር ለመገንባት እንደሚሰራ ተገልጿል። 

ከአርባምንጭና አከባቢዋ የተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች በመርሐ-ግብሩ ላይ በመገኘት ለእጩዎቹ ያላቸውን ድጋፍ እየገለጹላቸው ይገኛሉ። 

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያ በዲሞክራሲ ጎዳና የጀመረችውን ጉዞ የምታጸናበት ነው፣ የብልጽግና ጉዞ በህዝብ ይሁንታ ይቀጥላል፣ የህዝብ አገልጋይነት የአሸናፊነታችን ሚስጢር ነው፣ ለላቀ ድል በልማትና በዲሞክራሲ እንዘልቃለን፣ ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ  ፣የምርጫ ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው እነዚህንና ሌሎች መፈክሮች በአደባባይ ተስተጋብተዋል። 

#prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party