Prosperity Party

በአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች "የሴቶች ተሳትፎ ለተምሳሌታዊት ሀገር" በሚል መሪ ሀሳብ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ እና የምርጫ ምልክት ትውውቅ ፕሮግራም በድምቀት ተካሄደ

"የሴቶች ተሳትፎ ለተምሳሌታዊት ሀገር"

በአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች "የሴቶች ተሳትፎ ለተምሳሌታዊት ሀገር" በሚል መሪ ሀሳብ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ እና የምርጫ ምልክት ትውውቅ ፕሮግራም በድምቀት ተካሂዷል። 

በየመድረኮቹ የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ እና እኩልነትን በማረጋገጥ ረገድ ብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የአመራር ምደባ ታሪክ ውስጥ ሰፊ ድርሻ በመስጠት አዲስ ምእራፍ መክፈቱንና ይህንንም አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገልጿል።

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሻገርና  ለሀገር ግንባታ ሂደት  የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ ስለመሆኑ በስፋት ውይይት ተደርጓል።

በተለይም ብልፅግና ፓርቲ ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ቁርጠኛነት ያለው ፓርቲ በመሆኑ በመጪው ምርጫ በንቃት በመሳተፍ የተጀመረውን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገርነት ለማሻገር የሴቶች ሚና የማይተካ በመሆኑ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

#prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party