በብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ዋና ጽ/ቤት አስተባባሪነት በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ መድረኮች እየተካሄደ ይገኛል
በብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ዋና ጽ/ቤት አስተባባሪነት በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ መድረኮች እየተካሄደ ይገኛል።
የመድረኩ ዋና ዓላማ በባለፉት ሰባት ዓመታት በብልፅግና ፓርቲ የተሰሩ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር ውጤታማ ስራዎች፣ የተመዘገቡ ሀገራዊና ከባቢያዊ ልማቶች፣ የመልካም አስተዳደር፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ውጤቶችን ለማስቀጠል እና ሴቶች በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዘርፎች ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግ ለሀገር ግንባታ ያለው ፋይዳ በየደረጃው መግባባት ለመፍጠር ነው።
በየደረጃው እየተካሄደ ያለው ይኸው የንቅናቄ መድረክ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሴቶችን ሁሉ አቀፍ ተሳትፎ ለማሳደግ ታሳቢ ያደረገ መድረክ ነው።