Prosperity Party

በቡኖ በደሌ ዞን በደሌ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የ"ምረጡኝ" ቅስቀሳ ንቅናቄ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ደጋፊዎች በማሳተፍ በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ

በዚህ ታላቅ የሕዝብ ንቅናቄ መድረክ ላይ የተገኙት የከተማዋና የአካባቢው ነዋሪዎች ለፓርቲው ያላቸውን የማይናወጥ ድጋፍ ያሳዩ ሲሆን፣ መጪውን ብልጽግና ለማረጋገጥ ፓርቲውን ለመምረጥና የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት ሙሉ ቁርጠኝነታቸውን በተግባር አረጋግጠዋል።

በመድረኩ ላይ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነመራ ቡሊ ለተሳታፊዎች ቁልፍ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል። በንግግራቸውም ብልጽግና ፓርቲ በኢትዮጵያና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ የተመሠረተ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል።

ኃላፊው ፓርቲው የተመሠረተባቸውን ሦስት ዋና ዋና ግቦችና ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን በዝርዝር አብራርተዋል። የመጀመሪያው ግብ የትናንት ስህተቶችን ማረም መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ በአግላይነት የሚታወቀዉን የኢትዮጲያን ፖለቲካ አካታች እና ሁሉን ያቀፈ እና አሳታፊ እንዲሆን ማድረግ ሲሆን በመሆኑም ብልጽግና ፓርቲ ይህንን ሥር ነቀል በሆነ መልኩ በመለወጥና የመደመርን አስተሳሰብ በመያዝ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት፣ የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታት፣ የዴሞክራሲ ተቋማትን በማጠናከርና ፍትሐዊ ምርጫ እንዲካሄድ በማድረግ ረገድ ተስፋ ሰጪ ተግባራትን አከናውኗል። ይህም ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሥልጣን እንዲሳተፉና ብሔር ብሔረሰቦች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ዕድል ፈጥሯል።

ሁለተኛው ዋና ግብ ለአሁኑ ትውልድ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ሲሆን፣ ዜጎች ከድህነት የሚወጡበትን አጠቃላይና ሁሉን አቀፍ ፖሊሲዎችንና የከተማና የገጠር ትራንስፎርሜሽን ኢኒሼቲቮችን በመቅረጽ የክልሉና የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲሻሻል ተደርጓል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም እንዲፋጠን፣ የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ፣ የመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራር ችግሮች እንዲቀረፉ በርካታ እርምጃዎች ተወስደዋል። ዓለም አቀፍ ፈተና የሆነውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም በተሰሩ ሥራዎችም አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

ሦስተኛው ግብ የመጻኢውን ትውልድና የኢትዮጵያን የወደፊት ዕድል ማሳመር መሆኑን በመጥቀስ፣ የብልጽግና ፓርቲ የመደመር ጉዞ የመጨረሻ ዓላማ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሆነ አስገንዝበዋል። ፓርቲው ኢትዮጵያ የበለጸገች፣ የአፍሪካና የዓለም የብልጽግና ተምሳሌት የሆነች፣ ሉዓላዊነቷ የተከበረ፣ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ምንጭ እንዲሁም ለሌሎች የምትሰጥና የምትረዳ ሀገር እንድትሆን የማድረግ ራዕይ አለው።

ኃላፊው በንግግራቸው ማጠቃለያ ላይ፣ የተጀመረው ጉዞ የሚያሳየን በጠንካራ ሥራ ድህነትን የታሪክ ማድረግ እንደምንችልና ማንኛውንም ፈተና በድል መሻገር እንደምንችል ነው ብለዋል። ስለሆነም በአንድ በኩል የተገኙትን ስኬቶች ጠብቆ ማስቀጠልና ለተጨማሪ ድሎች በጋራ መቆም እንደሚገባ አሳስበዋል።
 ይህንንም እውን ለማድረግ በመጪው ምርጫ የብልጽግና ፓርቲን ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶን በመምረጥ፣ ለፓርቲው ድምፅ በመስጠትና ፓርቲው ያቀረባቸውን ዕጩ ተወዳዳሪዎች በሙሉ በመምረጥ የጀመርነውን የብልጽግና ጉዞ እንድናሳካ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በዕለቱ የቅስቀሳ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በርካታ ቁጥር ያላቸው የፓርቲው ደጋፊዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ የቀረበውን ሀገራዊና ክልላዊ የብልጽግና ራዕይ ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ ገልጸዋል። የተጀመሩ የልማትና የዴሞክራሲ ማሻሻያ ሥራዎች ከዳር እንዲደርሱ በመጪው ምርጫ የብልጽግና ፓርቲን ለመምረጥና የፓርቲውን ዕጩዎች በሙሉ ወደ ሥልጣን ለማምጣት ቃል በመግባት ታላቅ ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል።

 ነዋሪዎቹም የምርጫው ዕለት እስኪደርስ ድረስ የ"ምረጡኝ" ቅስቀሳውን በንቃት በማገዝ የድርሻቸውን እንደሚወጡና ድምፃቸውንም ለስንዴው ነዶ በመስጠት የሀገሪቱን ብሩህ ተስፋ እንደሚያረጋግጡ በታላቅ መነሳሳት ገልጸዋል።

#prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party