Prosperity Party

በሸገር ከተማ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ምረጡኝ የቅስቀሳ ንቅናቄ በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
በሸገር ከተማ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ምረጡኝ የቅስቀሳ ንቅናቄ በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።
ብልፅግና ፓርቲ ተዘንግቶ የነበረዉን ሀገራዊ አንድነት በማጠናከር፣ በሀገሪቱ ውስጥ ግጭቶችን የሚያባብሱ የተሳሳቱ ትራክቶችን በጋራ ትርክት በመተካት፣ የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ኢትዮጵያን እየገነባ ይገኛል።
የኦሮሚያ ጨፌ አፈ-ጉባኤ ክብርት ወይዘሮ ሳዓዳ አብዱራህማን በሸገር ከተማ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ እየተካሄደ ባለው የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት እንደገለጹት፤ ብልፅግና ፓርቲ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅና በርካቶችን ደግሞ በማስጀመር የኢትዮጵያን ከፍታ እያረጋገጠ እንደሚገኝና በፓርቲያችን መሪነት በተሰሩ የልማት ስራዎች ኢትዮጵያ የአፍሪካውያን የብልፅግና ምሳሌ እየሆነች ነው ብለዋል።
ብልፅግና ፓርቲ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሰነቀውን ራዕይ ለማሳካት በሁሉም ረገድ እየሰራ ባለው ስራ ከፍተኛ ስኬት እየተመዘገበ መሆኑን የገለፁት ወይዘሮ ሳዓዳ ህዝቡም ይህንን የስኬት ጅማሮ ለማስቀጠል በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለብልፅግና ፓርቲ ድምጹን እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።
ብልፅግናን ይምረጡ!
የምርጫ ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party