በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም ከተማ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ ዞናዊ የምርጫ ምልክትና እጩ ትውውቅ ፣የምርጫ ቅስቀሳ እና ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም ከተማ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ ዞናዊ የምርጫ ምልክትና እጩ ትውውቅ ፣የምርጫ ቅስቀሳ እና ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
በድጋፍ ሰልፉ የክልል፣የዞን፣የፍኖተሰላም ከተማና የጃቢ ጠህናን ወረዳ አመራሮችና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
በዚህ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፉ የተገኙት የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባይ አለሙ ለታዳሚዎች ባስተላለፉት መልዕክት ብልጽግና ፓርቲ በሁሉም ዘርፎች ስኬቶችን በማስመዝገብ የሀገሪቱን የሽግግር ጉዞ እያሳካ ይገኛል ብለዋል።
ምርጫችሁ ብልጽግና ሲሆን፣ እናንተ የምትመርጡት ጊዜያዊ መፍትሄን ሳይሆን ለልጅ ልጆቻችሁ የምትተርፍ የበለፀገችና የተከበረች ሀገርን ነው ሲሉም አስገንዝበዋል።
ብልፅግና ፓርቲ ለዘመናት ለትውልድ ሲንከባለሉ የነበሩ የዲሞክራሲ፣የእኩልነትና የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎችን በመደመር እሳቤ የመለሰ የህዝብ መሰረት ያለው ፓርቲ መሆኑን አብራርተዋል።
ፓርቲው በዞኑ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያስመዘገባቸውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት ስኬቶች አብራርተዋል።
ብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን ትናንትን በማከም፤ነገዋን በመትለም በትጋት እየሰራ ያለ ፓርቲ መሆኑ ተገልጿል።
ብልፅግና ፓርቲ ለዘመናት ለትውልድ ሲንከባለሉ የነበሩ የዲሞክራሲ፣የእኩልነትና የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎችን በመደመር እሳቤ የመለሰ የህዝብ መሰረት ያለው ፓርቲ መሆኑን አብራርተዋል።
ብልጽግና ፓርቲ የህብረ ብሔራዊነትና አንድነትን በማጽናት እየሰራ ያለ ግዙፍ ሀገራዊ ፓርቲ ነው።ፓርቲው ግጭትና ጦርነት የሚቀርበትን ስርዓት ለመገንባት በትኩረት እየሰራ መሆኑም ተገልጿል።
ብልፅግና ፓርቲን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!