በምርጫ ወቅት የሴቶች ተሳትፎ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ መሠረት ነው
ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኢትዮጵያ የታየው የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ፣ ከቁጥር ባለፈ የጥራትና የውሳኔ ሰጪነት ለውጥ የታየበት እንደሆነ መካድ አይቻልም።
ይህ እርምጃ ሀገሪቱ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና ለሁለንተናዊ እድገት የምታደርገውን ጉዞ የሚያፋጥን ትልቅ ምዕራፍ ነው።
ሴቶች በቁጥር የህብረተሰቡን ግማሽ ያህል የሚሸፍኑ እንደመሆናቸው መጠን፣ በምርጫ ሂደት ያላቸው ንቁ ተሳትፎ የፖለቲካ ውሳኔዎች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያካተቱ እንዲሆኑ ያስችላል።
ቀደም ሲል ሴቶች በብዛት የሚመደቡት በረዳትነት ወይም ማህበራዊ ዘርፎች ላይ ነበር። አሁን ግን እንደ መከላከያ፣ የጤና ሚኒስተር ፣የከተማ ልማት ሚኒስተር፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስተር ፣ የፍትህ ሚኒስቴር ፣የፕላንና ልማት ሚኒሰትር፣ የቱሪዝም ሚኒስተር ባሉ ስልታዊ በሆኑ የሀገር ደህንነትና ፖሊሲ ቀራጭ ተቋማት ላይ መሪነታቸውን አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ 50 በመቶ የሚሆነውን የካቢኔ ቦታ ለሴቶች በመስጠት በአፍሪካም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ አርአያ መሆን ችላለች።
በምርጫ ወቅት የሴቶች ግንባር ቀደም ተሳትፎ ሲባል ድምፅ ከመስጠት ባለፈ፣ በሂደቱ ውስጥ እንደ መሪ፣ ውሳኔ ሰጪ እና የለውጥ አነሳሽ የመሆን ሚናን ያካትታል።
እንኳን ለአለም አቀፍ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ !!