በማህበራዊ ሚዲያ የምናጋራቸው መረጃዎች ይዘት ከፓርቲ እሳቤዎችና አሰራሮች ጋር የተስማማ መሆን አለበት- የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ደስታ ተስፋው (ዶ/ር)
የብልፅግና የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ዋና ጽ/ቤት ለክልሎች ፣ለከተማ አስተዳደር ፣ፌተአ ብልጽግና የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን አባላት እና ለዞን ልዩ ወረዳና ከተማ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች 6ኛ ዙር በአዳማ ከተማ ለ3 ቀናት ሲሰጥ የነበረው ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረክ ተጠናቀቀ ።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ደስታ ተስፋው (ዶ/ር)
የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በድህረ እውነት ዘመን በሚል ስልጠና ሰጥተዋል።
በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መልዕክቶች የብልጽግና ፓርቲ መርሆችና እሴቶች ላይ የተመሠረቱ ፤ከህዝብ መልካም ባህልና እሴት ጋር የማይቃረኑ የትስስር ትርክትን መሠረት ያደረገ፤ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የወል እውነት ለማፅናት የሚረዱ ሊሆን ይገባል ተብሏል ።
የኮሚሽኑ ተግባርና ሀላፊነት እንዲሁም የአሰራር መመሪያዎችንና እቅዶችን ለማስተዋወቅ ሶሻል ሚዲያ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ጠቅሰዋል።
ደስታ ተስፋው (ዶ/ር) አክለውም እንደገለፁት በማህበራዊ ሚዲያ የሚጋሩ መረጃዎች ፓርቲው ከቆመላቸው አላማዎች ጋር የማይጋጩ መሆናቸውን ማረጋገጥ በህዝብ ዘንድ ያለውን አመኔታ ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተለያዩ መድረኮች የሚሰራጩ መልእክቶች ወጥነት እንዲኖራቸው ማድረግ፣ በደጋፊዎችና በአባላት ዘንድ ሊፈጠር የሚችልን ብዥታ ለመከላከል ይረዳል ብለዋል ።
ማህበራዊ ሚዲያ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን የሚቀንስና መልካም እድሎችን በአግባቡ ለመጠቀም በሚያስችል ሁኔታ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።
የኮሚሽኑ ፀሐፊና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ የስልጠናው ዓላማ በፓርቲውና በኮሚሽኑ የአሰራር ሥርዓቶች ላይ ግንዛቤ ከመፍጠሩም በተጨማሪ ሰልጠኙ እርስ በርሱ የልምድ ልውውጥ ማድረግ እንዲሁም በቀጣይነት በትኩረት ሊሰሩ የሚገባቸው ጉዳዮች መለየት በማስቻሉ ስልጠና የተሳካ መሆኑን አንስተዋል ።