Prosperity Party

በሁሉም መስክ የተጀመሩ መልካም አፈጻጸሞችን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባ ተገለጸ

የፌደራል ተቋማት ብልጽግና የፓለቲካ ዘርፍ የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ  አካሂዷል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል፤ የብልፅግና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር እና የፌዴራል ተቋማት ሰብሳቢ  አቶ ፍቃዱ ተሰማ  ለጠንካራ  መንግሥት የጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት ወሳኝ መሆኑን  ጠቅሰዋል።

የፌዴራል ተቋማት አደረጃጀት አብዛኛው የሀገሪቱ ከፍተኛ አመራሮችና ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማሳካት የሚተጉ ቁልፍ ተቋማት  የሚገኙበት መሆኑን ጠቅሰው የእስከ አሁኑን አፈጻጸም ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባ ተናግረዋል። 

በቀሪ ወራት ክላስተሮች በዘርፉ የሚጠበቅባቸዉን ሚና በመወጣት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ይበልጥ ማጎልበት ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የፌዴራል ተቋማት የፖለቲካ ዘርፍ ሰብሳቢ ተስፋዬ በልጅጌ(ዶ/ር)  በበኩላቸው በ6 ወራት በፖለቲካ ሥራዎች በታዩ መልካም አፈጻጸሞች መዘናጋት እንደማይገባ ተናግረዋል።

በአመራርና አባላት አቅም ግንባታ፤ ተግባራትን በእቅድ በመምራት፤ የመደበኛና የፓርቲ ሥራን አቀናጅቶ በመተግበር ያለው አፈጻጸም መልካም መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ተስፋዬ በቀሪ ወራት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን አስጠብቆ ማስቀጠልና ድክመቶች ላይ በትኩረት በመስራት በሁሉም መስክ እስከ አሁን የተመዘገቡ ውጤታማ አፈጻጸሞችን  ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባ ጠቅሰዋል። 

በመድረኩ የአስተዳደር፣ የኢኮኖሚ  እንዲሁም ማህበራዊ ክላስተር የዘርፉን የ6ወር አፈፃፀም አቅርበዋል።

የአፈጻጸም ግምገማ መድረኩ የፌዴራል ተቋማት፣ የክላስተሮች እና የወረዳዎች  አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party