በሀገራችን የዴሞክራሲ ባህል ለመገንባት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብርና በቅንጅት መስራት ይገባል-የብልጽግና ፓርቲ ዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ
ጥር 03 2018 ዓ.ም
ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየዉ የብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተጠናቀቀ።
በማጠቃለያ መድረኩ ላይ በሀገራችን የዴሞክራሲ ባህል ለመገንባት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብርና በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅ የተመላከተ ሲሆን የመጀመሪያ ስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረኩም ለበጀት አመቱ የተቀመጡ ግቦችን ማሳካት በሚያስችል ደረጃ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ማረጋገጥ እንዳስቻለ እና በቀሪዎቹ ስድስት ወራት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ደግሞ በላቀ አፈፃፀም መወጣትም በየደረጃው የሚገኙ አመራርና አባላት ሃላፊነት መሆኑን በማስታወስ በሌሎች ባለድርሻ አካላት የተጀመረዉ በትብብርና በቅንጅት የመስራት ባህልም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።
የግምገማ መድረኩ እንዳበቃ የዘርፉ አመራሮች ለነገዋ የሴቶች ተሃዲሶ እና ልህቀት ማዕከልን እና የአይነ ስውራን ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትን ጎበኝተዋል። ለነገዋ የሴቶች ተሃዲሶ እና ልህቀት ማዕከል ለተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የተጋለጡ ሴቶችን በስነ-ልቦ ተሀድሶና በሞያ ልህቀት በማብቃት ስራ ፈጣሪያዎች ሆነዉ ራሳቸውንና ሀገራቸውን የመለወጥ ራዕይን በማንገብ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተገንብቶ የበርካቶችን ህይወት በተጨባጭ እየቀየረ የሚገኝ ፕሮጀክት ሲሆን የአይነ ስውራን ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ደግሞ ማየት ለተሳናቸው ወገኖች የትምህርት ብርሃን በመፈንጠቅ በሀገራቸው ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት እና በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽ/ቤት በኩል ተገንብቶ መጠነ ሰፊ አገልገሎቶችን እየሰጠ የሚገኝ ተቋም እንደሆነ ይታወቃል።