ሴቶች የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ የጀርባ አጥንት ናቸው!
ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች እኩልነትና ተሳትፎ ለሀገር ብልፅግና ወሳኝ መሆኑን በጽኑ ያምናል። ይህ እምነት በንግግር ብቻ ሳይሆን በተግባር የታየበትን ምዕራፍ ተሻግረናል። በሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ፓርቲያችን ሴቶችን የማህበራዊና ፖለቲካዊ ለውጡ ግንባር ቀደም ተዋንያን እንዲሆኑ የሚያስችል ጽኑ አቋም ይዞ ቀርቧል።
ባለፉት የለዉጥ ዓመታት ባከናወናቸው ተግባራት በፌዴራል ደረጃ የሴቶች የውክልና ድርሻ 41.99 በመቶ ደርሷል። ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ስኬት ነው! በክልል ምክር ቤቶችም የሴቶች ተሳትፎ 44.7 በመቶ መድረሱ ፓርቲያችን ለሴቶች አመራርነት የሰጠውን ትልቅ ስፍራ ያሳያል።
በኢኮኖሚውም ዘርፍ ከ6.6 ሚሊዮን በላይ ሴቶች የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እንዲያገኙ በማድረግ የሀብት ባለቤትነታቸውን አረጋግጠናል። የፋይናንስ ተጠቃሚነትን በተመለከተ: የባንክ ሂሳብ ያላቸው ሴቶች ቁጥር ወደ 42.7 በመቶ ከፍ እንዲል በማስቻል ሴቶች የራሳቸውን የንግድ ስራ እንዲመሩ በር ከፍተናል።
በቀጣይም ፓርቲያችን የሴቶችን የፖለቲካ ውክልና ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለማድረስ ይሰራል። የሴቶችን የኢኮኖሚ አቅም ለመገንባት "ልዩ የብድርና የፋይናንስ ድጋፍ ስርዓት"ን እናጠናክራለን። ማንኛውንም አይነት ጾታዊ ጥቃት እና ኋላ ቀር ልምዶችን በማስወገድ ሴቶች በእኩልነት የሚኖሩባት ሀገር እንገነባለን።