Prosperity Party

ሴቶች የአገራችንን ሰላም በመጠበቅና በማስጠበቅ እያደረጉት ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክረው መቀጠል አለባቸው፡፡ ወ/ሮ ዘሀራ ሁመድ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ፕሬዝዳንት

የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ሀገርአቀፍ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የማኒፌስቶና ምርጫ ምልክት የማስተዋወቂያ መርሃ ግብር አካሄዷል።

የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሀራ ሁመድ በመርሃ ግብሩ እንደገለጹት ሴቶችን የአገራችንን ሰላም በመጠበቅና በማስጠበቅ ከፍተኛ ድርሻ ስላላቸው ከቤት እስከ ምርጫ ጣቢያ እንዲሁም አገራዊ ሰላም ለማስፋን የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል፡፡ 

ባለፉት ስምንት ዓመታት ተጨባጭ ለውጥ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት መመዝገቡን የገለጹት ፕሬዘዳንቷ ዕድሜው ለመምረጥ የደረሰ ሁሉም ኢትዮጵያዊ  ህገ መንግስታዊ መብቱን እንዲጠቀም ለማድረግ ሴቶች በየአደረጃጀት በንቅናቄ  ሊሳተፉ ይገባል ብለዋል።

የአገራችንን ሰላም ከማስጠበቅ ጎን ለጎን በምርጫ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት እንደሆኑ ማሳየት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል፡፡ 

የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዘዳንትና የፅ/ቤቱ ሃላፊ ወ/ሮ መስከረም አበበ በበኩላቸው የፓርቲውን እሳቤዎች፣ ስኬቶች እንዲሁም የወደፊት ትልም በሚገባ ለማስረፅ በየአደረጃጀት ከሚካሄደው ስልጠና ባለፈ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተሳትፎን በማጠናከር በጉልህ መታየት ይገባል ብለዋል። 

ሴቶች ምርጫው ሰላማዊ ዴሞክራሲያና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሴት አደረጃጀት በተቀናጀና በተናበበ ሁኔታ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በመስራት የምርጫ ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን በንቅናቄ መሳተፍ ይገባል፡፡ 

የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ምክትል ፕሬዘዳንት ወ/ሮ ጠኢባ ሃሰን እንደገለፁት ሴቶች አደረጃጀትን በተቀናጀ መንገድ በመጠቀም ክንፉ ሃላፊነቱን እንደሚወጣም ገልፀዋል። 

የፓርቲው መመሪያዎችና አቅጣጫውችን እስከታችኛው አደረጃጀት በማውረድ ለተግባራዊነቱ መትጋት ያስፈልጋል ነው ያሉት። 

በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ የነበራቸውን ንቁ ተሳትፎ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መድገም እንደሚገባም ገልፀዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party