ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአቪዬሽን ኤክስፖን ጎበኙ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ 90ኛው የአየር ኃይል ቀንን በማስመልከት የተዘጋጀውን የአቪዬሽን ኤክስፖ ተገኝተዉ ጉብኝት አካሂደዋል።
በጉብኝቱም: በተለያዩ የአቪዬሽን ትጥቅ አምራች ኩባንያዎች የተመረቱ፣ የዘመኑ የአለም አቭዬሽን ቴክኖሎጂ የደረሰበትን የልቀት ደረጃ የሚያሳዩ፣ የውጊያ የበላይነትን የሚያረጋግጡ፣ የመፈፀም አቅምን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ የተለያዩ የአቭዬሽን ምርቶችንና ትጥቆችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።