Prosperity Party

መጋቢት 24 የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ከፍታ ጅማሮ

መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም የለውጡ መንግሥት ሀገራዊ ኃላፊነትን የተረከበበት ታሪካዊ ቀን ሲሆን፣ በተለይም በውጭ ግንኙነትና በዲፕሎማሲው ዘርፍ አዲስና ብሩህ ምዕራፍ የተበሰረበት ዕለት ነው፡፡ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት ኢትዮጵያ የነበረባትን የዲፕሎማሲ ከበባ በመስበርና ብሔራዊ ጥቅሟን በማስከበር ረገድ እመርታ የታየባቸው ስኬቶች ተመዝግበዋል፡፡ 

የለውጡ መንግሥት ለጎረቤት አገራት ቅድሚያ የመስጠት መርሕን በመከተል በቀጣናው ከጥርጣሬ ይልቅ በትብብርና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ጠንካራ ትስስር እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ ይህም ኢትዮጵያን የታሪካዊ ጠላቶቻችንን ከበባ እንድትሰብር ከማድረጉም ባለፈ፣ በመሠረተ ልማትና በታዳሽ ኃይል አቅርቦት አማካኝነት የአገራችንን ቀጣናዊ ተፅዕኖ በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል፡፡

የአገራችን ዲፕሎማሲያዊ ጉዞ ከጎረቤት ባለፈም በዓለም አቀፍ መድረክ የገለልተኝነትን መርሕ በመከተልና ብሔራዊ ጥቅምን በማስቀደም ውጤታማ የኹለትዮሽና ባለብዙ ወገን ግንኙነቶችን መፍጠር ችሏል፡፡ ኢትዮጵያ ለገጠሟት ውስብስብ ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ፈተናዎች እጅ ሳትሰጥ፣ ችግሮችን ወደ ዕድል የመለወጥ ብቃቷን በማሳየት በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነትና የዲፕሎማሲ አቅም አጠናክራ ቀጥላለች፡፡ 

በተለይም ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን እንደ አንድ ትልቅ ምሰሶ በመውሰድ፣ ዲያስፖራው እንደ ስጋት ከመታየት ወጥቶ እንደ ትልቅ ቤተሰብና የአገር ኩራት እንዲቆጠር ተደርጓል፡፡ በዚህም በውጭ አገራት የሚኖሩ ዜጎች ክብራቸውና መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖር ከማስቻሉም በላይ፣ ዲያስፖራው በባለቤትነት ስሜት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ጎን እንዲቆም በማድረግ ረገድ ታላቅ ድል ተመዝግቧል፡፡ በአጠቃላይ መጋቢት 24 ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ የከፍታ ጉዞዋን የጀመረችበትና የአገራዊ ኩራት ምንጭ የሆነችበት ልዩ ቀን ነው፡፡

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party