ለሰላማዊ ምርጫ የሴቶች ሚና የላቀ ነው!
እንኳን ለዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ
ሴቶች ከልጅ እስከ ቤተሰብ፣ ከማህበረሰብ እስከ ሀገር
በማስተዋል የተቃኘ፣ በጥበብ የታነፀ አበርክቶ አላቸው።
በጥበብ ቤቷን የምትመሰርት፣ ልጆችን በማስተዋል የምታሳድግ እና ሀገርን በረቂቅ ፍልስፍናዋ የምትመራ የማህበራዊ ህይወት መሰረት ናት ሴት።
ሴቶች በአለምም ይሁን በሀገር ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ፤ በሰላም እና በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ግንባር ቀደም ሚና በመጫወት ለሀገር ሁለንተናዊ ብልፅግና የድርሻቸውን ይወጣሉ።
ይህንን የሴቶች ጉልበት፣ ጥረት እና ስኬት ለማስታወስ ማርች 8 /የካቲት 29 – ዓለም አቀፍ የሴቶች በየዓመቱ ይከበራል። ይህ ቀን የሴቶችን መብት፣ እኩልነት እና ክብር ለማሳደግ የሚያስታወስ ቀን ነው።
ሴቶች በሀገራዊ ምርጫ ላይ ያላቸው ተሳትፎ ለዴሞክራሲ እና ለሀገር እድገት ወሳኝ ነው። ሴቶች እንደ መራጭ በመሆን ድምፃቸውን በመስጠት ወይም እንደ እጩ በመቆም በሀገር አስተዳደር ላይ ያላቸውን ሚና ማጠናከር እንደሚችሉ አሳይተዋል።
ሴቶችን በምርጫ ሂደት ላይ ማበረታታት እና እኩል ዕድል መስጠት ዴሞክራሲን ለማጠናከር አስፈላጊ ነው። የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ተዓማኒ እንዲሆን፤ ፓርቲያችንም ቅቡልነት አግኝቶ በአሸናፊነት እንዲያጠናቅቅ ሴቶች የሚያበረክቱት ሚና ከፍ ያለ ነው። የፓርቲያችን መንታ ግቦች እንዲሳካ በማድረግ ረገድ የማይተካ ድርሻ ስለሚኖራቸው የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ይገባል።
ፓርቲያችን ብልፅግና የሴቶችን እምቅ አቅም ተረድቷል።
ቤተሰብን ማህበረሰብንና ሀገርን ያቆመችበትን ተፈጥሯዊ ፀጋ በሚገባ ተገንዝቧል። የሀገርን ሁለንተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥ ያለሴቶች ተሳትፎ የማይታሰብ መሆኑን አውቋል። በፓለቲካ የሚኖራቸውን ተሳትፎ 50 በመቶ በማሳደግም ከአህጉር ተሻግሮ ለአለም ተሞክሮ መሆን ተችሏል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት የሴቶችን ተጠቃሚነት ማሳደግ የተቻለ ሲሆን÷ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሴት ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሴቶችን ወደ አመራርነት ማምጣት ተችሏል። እንዲሁም 50 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች የካቢኔ አባላት ሆነው ቁልፍ ሴክተሮችን እንዲመሩ ተደርጓል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሁን ላይ ሴቶች 41 በመቶ የሚሆነውን መቀመጫ አግኝተው የወከላቸውን ማሕበረሰብ እያገለገሉ ነው።
በማሕበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል።
የዘንድሮውን አለምአቀፍ የሴቶች ቀን ስናስታውስ በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ በእጅጉ የጨመረውን የሴቶች ተሳትፎ እውቅና በመስጠት ነው። በተጨማሪም ለምርጫው ስኬት ያላቸውን አስተዋጽኦ እንዲወጡ በማሳሰብ ነው።
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!