ለመምረጥ_እሮጣለሁ፤ ሠላሜንም እጠብቃለሁ!
ብልጽግና ፓርቲ ለ7ኛዉ ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫን አስመልክቶ የተካሄደ የጎዳና ላይ ሩጫ ዉድድር በሸገር_ከተማ አካሂዷል፡፡
7ኛው ዙር አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሠላማዊ፣ ዴሞክራሲአዊ፣ ነፃ፣ ፍትሐዊና ሁሉንም ያሳተፈ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በሁሉም አቅጣጫ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ፍትሐዊና ዴሞክራሲአዊ የሆነ ምርጫ እና ሠላማዊ የስልጣን ሽግግር የተለመደ ባለመሆኑ እስካሁን ጠንካራ የሆነ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እና በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መንግስት ማቋቋም ሳይቻል ቆይቷል። ይህም በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ አለመረጋጋትን አስከትሎ አገሪቷ አሁን ላለችበት ሁኔታ እንድትዳረግ አድርጓታል።
ከሽግግሩ ወዲህ ግን የመደመር መንግሥት 6ኛው ዙር አጠቃላይ አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና አሳታፊ እንዲሆን በማድረግ በሕዝቡ ዘንድ ቅቡልነት ያለው መንግሥት እንዲቋቋም በማድረግ በዚህች አገር የምርጫ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት ችሏል።
በዚህ ዓመት ግንቦት 24/2018 ዓ/ም የሚደረገው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ከቀደሙት ጊዜያት በበለጠ ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ አሳታፊ እና ሰላማዊ እንዲሆን ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ስለህነ ለስኬታማነቱ የሁሉም ሰው ሚና ወሳኝ መሆኑ ይታመናል።
የዘንድሮውን የብልፅግና ፓርቲ የምረጡኝ ዘመቻን አስመልክቶ በሸገር ፉሪ ክ/ከከተማ "ለመምረጥ እሮጣለሁ፤ ሠላሜንም አስጠብቃለሁ" በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን እና የሲቪል ማሕበረሰቦችን ያሳተፈ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሂዷል፤ ፕሮግራሙ ሰላማዊ ምርጫን ለማረጋገጥ የሁሉም ሰው ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን እና ሁሉም ሰው የራሱን ሚና መጫወት እንዳለበት መልእክት ለማስተላለፍ ያለመ ነው።
ብልፅግናን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
#Prosperity