ሃገራዊ ለዉጡን የሚዘክሩ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፎች ተካሄዱ ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት የሚዘክር ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተካሂዷል። የሰልፉ ተሳታፊ የሆኑ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉት መጋቢት 24 የሃገራችን ተምሳሌታዊ ጉዞ እና የተመዘገቡ ስኬቶች መነሻ ነዉ። በለውጡ መንግሥት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራትን በመደገፍ፣ በቀጣይም የተሻለ ስራ እንዲሰራ ከመንግሥት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ የሚያረጋግጡ መልዕክቶችነም አስተላልፈዋል። በሰልፎቹ ላይ ከተስተጋቡ መፈክሮች መካከል: በመጋቢት 24 ፍሬ ወደ ተምሳሌታዊ ጉዞ፣ ጠንካራ መሰረት የተምሳሌትነት ጉዞ ስንቅ፣ መሰረት ባለው ርምጃ ወደ ተምሳሌትነት፣ መጋቢት 24 የተምሳሌታዊነታችን መሰረትና መፍለቂያ ነው፣ መጋቢት 24 ሀገር ከመፍረስ የዳነችበት የታሪክ ምዕራፍ የሚሉ ይገኙበታል። ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሃገር!
ሃገራዊ ለዉጡን የሚዘክሩ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፎች ተካሄዱ
ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት የሚዘክር ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተካሂዷል።
የሰልፉ ተሳታፊ የሆኑ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉት መጋቢት 24 የሃገራችን ተምሳሌታዊ ጉዞ እና የተመዘገቡ ስኬቶች መነሻ ነዉ።
በለውጡ መንግሥት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራትን በመደገፍ፣ በቀጣይም የተሻለ ስራ እንዲሰራ ከመንግሥት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ የሚያረጋግጡ መልዕክቶችነም አስተላልፈዋል።
በሰልፎቹ ላይ ከተስተጋቡ መፈክሮች መካከል: በመጋቢት 24 ፍሬ ወደ ተምሳሌታዊ ጉዞ፣ ጠንካራ መሰረት የተምሳሌትነት ጉዞ ስንቅ፣ መሰረት ባለው ርምጃ ወደ ተምሳሌትነት፣ መጋቢት 24 የተምሳሌታዊነታችን መሰረትና መፍለቂያ ነው፣ መጋቢት 24 ሀገር ከመፍረስ የዳነችበት የታሪክ ምዕራፍ የሚሉ ይገኙበታል።
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሃገር!