ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በሳጃ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ አካሄደ
ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በሳጃ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ አካሂዷል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በየም ዞን ሳጃ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
በህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር )የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ እጅጉ፣ የክልል፣የየም ዞን የስራ ኃላፊዎች እና የብልጽግና ፓርቲ ደጋፊ አባላት ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሔደ በሚገኘው ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ምርጫዬ ብልጽግና ነው፣የምግብ ሉአላዊነት ተምሳሌት፣በዲጂታል ኢትዮጵያ ነገን መገንባት፣ጸጋን ወደ ሀብት፣ብልጽግናን እመርጣለሁ አሻራዬን አኖራለሁ፣ትላንትን ማከም ነገን መተለም እና ሌሎችም መፈክሮች ተስተጋብተዋል።
#prosperity