Prosperity Party

ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በቆሼ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8 ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በማረቆ ልዩ ወረዳ በቆሼ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው

በድጋፍ ሰልፉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (/)በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ /ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ( /)የማረቆ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አማሮ፣የክልል፣የልዩ ወረዳው ከፍተኛ አመራሮች እና የብልጽግና ፓርቲ ደጋፊ አባላት ተገኝተዋል።

በድጋፍ ሰልፉ ምርጫዬ ብልጽግና ነው፣የምግብ ሉአላዊነት ተምሳሌት፣በዲጂታል ኢትዮጵያ ነገን መገንባት፣ጸጋን ወደ ሀብት፣ብልጽግናን እመርጣለሁ አሻራዬን አኖራለሁ፣ትላንትን ማከም ነገን መተለም እና ሌሎችም መፈክሮች ተስተጋብተዋል።

#prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party