Prosperity Party

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ እንዲሆን ሴቶች በግንባር ቀደምነት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል። አቶ አደም ፋራህ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዘዳንትና የ ዋና ፅ/ቤት ኃላፊ

የሰላም ሚኒስቴር ከሴቶች አደረጃጀት ጋር በመተባበር
"ለሰላማዊ ምርጫ የሴቶች ሚና" በሚል መሪ ሃሳብ አገር  አቀፍ የማጠቃለያ መድረክ አካሄደ።

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዘዳንትና የዋና ፅ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አደም ፋራህ  በማጠቃለያ መድረክ እንደገለፁት  7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ እንዲሆን እና ዴሞክራሲ እንዲያብብ ሴቶች እንደመራጭ ፤ እንደተወዳዳሪ ፤ እንደሰላም ዘብ በመሆን አሻራቸውን በግንባር ቀደምነት ሊያኖሩ ይገባል።

በለውጥ ማግስት ሴቶች በመንግስት ስልጣን ከ50 በመቶ በላይ ድርሻ እንዲኖቸው በማድረግ አለምአቀፍነት ያለው ተምሳሌትነት ተመዝግቧል ብለዋል።

በኮሪደር ልማት፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በሌማት ትሩፋት እና በመሳሰሉ የመንግስት ኢኒሼቲቮች ግንባር ቀደም ተጠቃሚና ተሳታፊ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

ቁልፍ የውሳኔ ሰጪ ተቋማት በሴት አመራሮች እንዲመሩ መደረጋቸው የለውጡን ፍሬያማነት ማሳያ ነውም ብለዋል።

የመምረጥና የመመረጥ መብትን በመጠቀም የፓለቲካ ስልጣን ባለቤት መሆናቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባም ጠቅሰዋል። 

ሴቶች የምርጫውን ሰላማዊነት ከማስጠበቅ ባለፈ በሀሳብ ልዕልና ላይ የተመሠረተ እንዲሆን  ማስቻል ይገባል ብለዋል።

ወጣቱ በምርጫው ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ የማስተማር ሃላፊነታቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።

በኢ.ፈ.ዲ.ሪ ሰላም ሚንስቴር እና  ከብልፅግና ሴቶች ክንፍ ጋር በመተባበር በሴቶች ተሳትፎ የጸናችና የበለጸገች ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል ከፌዴራል እስከ ቀበሌ ሲካሄድ የነበረዉ የንቅናቄ መድረክ በተለያዩ ኩነቶች ታጅቦ ከጫፍ እስከ ጫፍ በድምቅት ተካሂዶ በዛሬው እለት ተጠቃሏል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party