Prosperity Party

7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በማስመልከት በዲላ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ ተካሄደ

 የብልጽግና ፓርቲ በዲላ ከተማ ''ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል የ7ኛውን አገራዊ ምርጫ በሰልፍ የታጀበ ደማቅ ቅስቀሳ ተደርጓል።

በተካሄደው በዚህ የሰልፍ ቅስቀሳ ፓርቲው ባለፉት ዓመታት ያስመዘገባቸውን ስኬቶችና ለወደፊት የያዛቸውን የቀጣይ የልማት ዕቅዶች ለህዝብ ይፋ አድርጓል።

የምርጫ ቅስቀሳው ወቅት ፓርቲው በዲላና በአካባቢው የጀመራቸውን የመሠረተ ልማት፣ የግብርና ምርታማነትና የኢንዱስትሪ ግንባታ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

በከተማ የሚታየውን የህዝቦች አብሮነት ይበልጥ በማጠናከር፣ ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ አገረ መንግሥት ግንባታ ፓርቲው ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ቃል ገብቷል።

በከተማዋ ለሚገኙ ወጣቶችና ሴቶች የሥራ ዕድል ፈጠራንና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደሚተገበሩ ተመልክቷል።

በዕለቱ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው ተወካዮች፣ ብልጽግና ፓርቲ የህዝብን ጥያቄ መሠረት ያደረገ የለውጥ ጉዞ እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ ነዋሪው ለፓርቲው ምልክት ለሆነው የ''ስንዴ ነዶ''  ድምጹን በመስጠት የጀመረውን የብልጽግና ጉዞ እንዲያፋጥን ጥሪ አቅርበዋል።

የቅስቀሳ መርሃ-ግብሩ በዲላ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች በሰልፍ የታጀበ ሲሆን፣ በቀጣይ ቀናትም በከተማ በሚገኙ ሁሉም ክ/ከተማና ቀበሌ መዋቅር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ርዕሰ መስተደድርና ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር)፣ የከተማ ከንቲባ መስፍን ደምሴ (ዶ/ር)፣የወናጎ ምርጫ ክልል 2 ዕጩ ተወዳዳሪዎች፣ የከተማ አጠቃላይ አመራሮች፣ የፓርቲ አባላትና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ቅስቀሳ ተጀምሯል።

"ድምጽዎ ለብልጽግና፣ ድምጽዎ ለነገዋ የተሻለች ኢትዮጵያ!" የሚሉ መፈክሮች በከተማዋ አደባባዮች ሲስተጋቡ ውለዋል።

#ምርጫችን_የስንዴ_ነዶ_ነዉ 
#ብልፅግናን_ይምረጡ 
#ኢትዮጵያ_ወደ_ተምሳሌት_ሀገር

#prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party