7ተኛዉ ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫን በማስመልከት የዲላ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ አካሄደ
በዲላ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች፣ የፓርቲውን የድል ጉዞ ለማብሰርና የ7ኛውን አገራዊ ምርጫ ግብ ለማሳካት የሚያስችል ሰፊ የድጋፍና የቅስቀሳ መርሃ-ግብር በዛሬው ዕለት አካሂደዋል።
የቅስቀሳ መርሃ-ግብሩ ፓርቲው ለሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የነደፋቸውን ስትራቴጂዎችና የልማት እቅዶች ለነዋሪው ለማስተዋወቅ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ነዋሪው ለብልጽግና ፓርቲ ያለውን ድጋፍ በድምጹ እንዲያረጋግጥ ጥሪ ቀርቧል።
በመድረኩ ብልጽግና ፓርቲ ላለፉት ዓመታት የሴቶችን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ለማሳደግ የሰራቸውን ስራዎች በማጠናከር በቀጣይም ይበልጥ ውጤታማ የሆኑ ስራዎችን ለመስራት ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል።
የሴቶች ክንፍ አባላቱም በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የፓርቲውን ምልክትና ራዕይ በማስተዋወቅ ለ7ኛው አገራዊ ምርጫ የምረጡን ጥሪያቸውን በታላቅ ድምቀት የተለያዩ መልዕክቶችን በማስተላለፍ አስደምጠዋል።
በዲላ ከተማ የሚገኙ የሴቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች በፓርቲው መሪነት የተመዘገቡ ስኬቶች እንዲቀጥሉ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።
በቅስቀሳው ፕሮግራም ላይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዲላ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሴቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።