ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቱርክዬ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ረጅብ ጣይፕ ኤርዶዋን ያደረጉት አቀባበል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቱርክዬ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ረጅብ ጣይፕ ኤርዶዋን በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ይፋዊ ጉብኝት ዛሬ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል። ይህ ጉብኝት በቱርክዬ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን እያደገ የመጣ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚያጎላ ሲሆን፤ የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ሚናም የሚያረጋግጥ ነው።