በጋሞ ዞን ጨንቻ ምርጫ ክልል በሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ማኒፌስቶና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መድረክ ተካሄደ
በጋሞ ዞን ጨንቻ ምርጫ ክልል ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ በሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት በ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ማኒፌስቶና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መድረክ ተካሂዷል።
በወረዳው ሻማ ክላስተር የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አባላት "ጊስቴ ሚዲ ጊስቴ ዶራና" በሚል መሪ ቃል 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ማኒፌስቶና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መድረክ አካሂደዋል።
በመርሃ- ግብሩ የወረዳው አስተባባሪ አካላትና አመራሮች፣ የሴቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
#ኢትዮጵያ_ወደ_ተምሳሌት_ሀገር
#ምርጫ_2018
#ምልክታችን_የስንዴ_ነዶ_ነዉ
#ብልፅግናን_ይምረጡ
#prosperity