ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አዲሱን የአራዳ ፓርክ መረቁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት አዲሱን የአራዳ ፓርክ መርቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የአራዳ ፓርክ አዲስ አበባን ለመለወጥ ያለንን ርዕይ በተግባር ያሳየንበት አንዱ ስራችን ነው ብለዋል።
ቀደም ሲል ተዘንግቶና ለአደጋ ተጋልጦ የነበረው የአራዳ አካባቢ፣ ዛሬ ተመልሶ ተገንብቶ አስደናቂ የከተማ አካል መሆን መቻሉን ገልጸዋል።
"ኢትዮጵያ ለእኛ በምናብ የምትሳል ህልም ብቻ ሳትሆን በተግባር የምትገነባ እውነታ ናት" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ጤናማ፣ ጽኑ፣ ለመጭው ትውልድ ተስፋን ከተጨባጭ ሀብት ጋር የምትሰጥ፣ በአፍሪካ መሪ፣ በዓለም መድረክ ደግሞ ተወዳዳሪ የሆነች ሀገር እየተገነባች መሆኑን አስታውቀዋል።
መንግሥት በየቀኑ ይህንን ተስፋ ወደ እውነታ የመለወጥ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።