ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ በዓለ ሲመት ላይ ተገኙ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመራጩ የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌን የበዓለ ሲመት ሥነ ሥርዓት ለመታደም ዛሬ ጅቡቲ ተገኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ የተመራጩ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌን የበዓለ ሲመት ሥነ-ሥርዓት ለመታደም ዛሬ ጅቡቲ ተገኝቻለሁ ሲሉ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ለሃገራቸው የሚሰጡት አገልግሎት ሁለንተናዊ እድገትን እንዲያስቀጥል ልባዊ ደስታዬንና መልካም ምኞቴን ልገልጽ እወዳለሁ ብለዋል።
በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለው የቆየ ወዳጅነት እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለሕዝቦቻችን የጋራ ብልጽግና እንዲሁም ለቀጣናችን ሰላምና መረጋጋት መጠናከር መሰረት እንዲሆን እመኛለሁ ነው ያሉት።