Prosperity Party

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጀመሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት መጀመራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ገልጿል።

የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጠነከረ መጥቷል፤ ለዚህም ጉልህ ማሳያው በጠንካራ ትብብር የቀጠለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጎልቶ ይታያል። 

ይህንኑ ወደላቀ ደረጃ ያደገዉን የሁለቱ ሀገራት መቀራረብ ተከትሎም፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት መጀመራቸውን ነው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያስታወቀው። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር ዛሬ ረፋድ ላይ በባኩ ሄዳር አሊዬቭ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሳቸውም ተገልጿል። 

የአሁኑ ጉብኝት የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ ይሸጋግራል ተብሎ እንደሚጠበቅም አስታውቋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party