Prosperity Party

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለ አዲሱ አራዳ ፓርክ

የአዲሱ አራዳ ፓርክ ታሪክ ጥልቅ ለውጥ የታየበትና በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  በተገኙበት ይፋ የተደረገ ታላቅ ፕሮጀክት ነው። ቀደም ሲል ተዘንግቶ፣ ለአደጋ የተጋለጡ ቤቶች የነበረው ይህ 40 ሄክታር መሬት፣ ዛሬ ተመልሶ ተገንብቶ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ ቀዳሚ የከተማ መዳረሻ ሆኗል። ይህ ፕሮጀክት ፓርክ ብቻ ሳይሆን፤ የተቀናጀ መሠረተ ልማትና የመሬት አጠቃቀም ብቃት የታየበት ጥበብ ነው። ከ700 በላይ ነባር ቤቶችንና ሕንፃዎችን በማደስ፣ ልማቱ ማኅበረሰቡን 
የሚያገል ሳይሆን የሚያቅፍ እንዲሆን ተደርጓል።

• ለምለም የከተማ መናፈሻ
ከጠቅላላው 40 ሄክታር መሬት ውስጥ 15 ሄክታሩ በአረንጓዴ የተሸፈነ  ሲሆን፤ ይህም ለአዲስ አበባ መሀል እንደ መተንፈሻ ሆኖ ያገለግላል።

• ከተማን ማገናኘት
በዲዛይኑ ውስጥ ለእንቅስቃሴ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቷል፤ ይህም 5 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ፣ 6 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መሄጃ፣ እንዲሁም ለብስክሌትና ለሩጫ የሚሆኑ 5 ኪሎ ሜትር መንገዶችን ያካተተ ሲሆን፤ ይህም ጤናማና ንቁ የአኗኗር ዘይቤን ያበረታታል።

• የኢኮኖሚ ጥንካሬ
ፓርኩ ለንግድ እንቅስቃሴዎች ትልቅ ማዕከል ነው፤ ከፒያሳ ለተነሱ ነጋዴዎች ቅድሚያ የሚሰጡ 131 የንግድ ሱቆች፣ 7 ካፌዎችና ምግብ ቤቶች፣ ሱፐርማርኬትና የባንክ ቅርንጫፍ በመያዝ የኢኮኖሚ ዘላቂነትን ያረጋግጣል።

• ጤናና ባህል
ከአረንጓዴው ስፍራ በተጨማሪ ፓርኩ ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ፣ ጂምናዚየም እና 7 አዳራሾችን ይዟል። ከዚህም ጎን ለጎን ለዓለም አቀፍ ደረጃ ጥበባትና ለማኅበራዊ ኩነቶች የተዘጋጁ 8 አደባባዮችና አምፊቲያትሮችን አካቷል።

• ቤተሰብና ዘመናዊነት
ሕፃናት የሚጫወቱባቸው 4 ስፍራዎችና ልዩ የሆነ 'ትንሿ ከተማ' (Miniature City) ተገንብቶላቸዋል።

በፈጠራ የታጀበ ባለብዙ ወለል ዲዛይን በመጠቀም በግርማ ሞገስ በተገነቡ አደባባዮች ሥር ደማቅ የንግድ ስፍራዎችን በማካተት የአራዳ ፓርክ ውድ የሆነውን የከተማ መሬታችንን በእያንዳንዱ ስንዝር በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል አድርጓል።

The story of the newly inaugurated Arada Park is one of profound transformation, a landmark project officially unveiled today in the presence of Prime Minister Abiy Ahmed. What was once a 40-hectare area of neglected, hazardous, and dilapidated housing has been reimagined into a premier multi-purpose urban destination. This project isn’t just a park; it is a masterclass in integrated infrastructure and land-use efficiency. By renovating over 700 existing homes and buildings, we have ensured that development uplifts the community.

• A Green Urban Sanctuary
Out of the 40-hectare total area, 15 hectares have been dedicated to lush greenery, providing a vital "lung" for the heart of Addis Ababa.

• Connecting the City
Mobility is at the core of the design, featuring 5km of asphalt roads, a 6 km pedestrian walkway, and dedicated 5 km tracks for both cycling and running, encouraging a healthier, active lifestyle.

• Economic Vitality:

The park serves as a commercial hub with 131 business shops, prioritizing displaced traders from Piassa, 7 cafes and restaurants, a supermarket, and a bank branch, ensuring economic sustainability.

• Wellness and Culture
Beyond the greenery, the park houses a modern sports arena with a gym and 7 halls, alongside 8 plazas and amphitheatresdesigned for international-standard arts and social events.

• Family and Modernity:
Children can explore 4 playgrounds and a unique Miniature City

By utilizing innovative multi-level design, placing vibrant commercial shops beneath elegant public plazas, Arada Park maximizes every inch of our precious urban land.

#EthiopiaDelivers
#PMOEthiopia

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party