ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲት አቀባበል አደረጉ
የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ተቀብያለሁ። ይኽ ጉብኝት በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጠንካራ እና ዘላቂ ግኙነት የሚያሳይ ነው። ትብብራችንን እና የጋራ ፍላጎቶቻችን ለማጠናከር የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት እንደምናደርግ እምነቴ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)