የ2018 በጀት ዓመት ለፓርቲው በርካታ ፖለቲካዊ ድሎችና ዘርፈ ብዙ ስኬቶች የተመዘገቡበት ዓመት ነው
የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በውይይት መድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የዋና ጽ/ቤት የዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትሮች፣ ሚንስትር ደኤታዎች፣ የቅ/ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ሌሎች አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመድረኩ ላይ በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የስትራቴጂ ሥራ አመራርና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምን አቅርበዋል።
በአፈጻጸሙ መሠረት የ2018 በጀት ዓመት ለፓርቲው በርካታ ፖለቲካዊ ድሎችና ዘርፈ ብዙ ስኬቶች የተመዘገቡበት ዓመት እንደነበር ተጠቁሟል። በተለይም የ2018 ዓ.ም. መሠረታዊ አቅጣጫ የአሰራር፣ የዕቅድና የአፈጻጸም ስታንዳርዳይዜሽንን በማስፈን ውጤታማ ሥራ መከናወኑ ተገልጿል።
እንዲሁም በ2018 በጀት ዓመት ፓርቲው መደበኛ ተግባራቱን ከ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ጋር የተያያዙ ሁለት መንትያ ግቦችን በዋናው ጽሕፈት ቤትና በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በተደራጀና በተቀናጀ አሰራር በመምራት በምርጫው በአብላጫ ድምጽ ድል ማስመዝገቡ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህ(ዶ/ር) በቀጣይ ተቋማዊ አሰራር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ገለጻ አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ላይ ግምገማ ተካሂዶ፣ በቀጣይ የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይም ተሳታፊዎች ውይይት በማካሄድ ለአፈጻጸሙ የሚያግዙ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
#prosperity