የፓርቲው የምርጫ የአሰራር ሥርዓት መመሪያ ተፈፃሚነት በየደረጃው በሚገኙ የኮሚሽን መዋቅሮች ክትትል ተጠናክሮ መቀጠል አለበት-ደስታ ተስፋው (ዶ/ር) የኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር
የብልጽግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን በፓርቲው የምርጫ የአሰራር ስርዓት መመሪያ በተሰጠው ተግባራትና ኃላፊነት መሠረት የመመሪያውን አፈጻጸም ሂደት በ11 ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደር ባለፉት አሥር ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የኢንስፔክሽን ግኝቶች ሪፖርት ግምገማ አካሂዷል፡፡
በግምገማ መድረኩ ደስታ ተስፋው(ዶ/ር) የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር እንደገለጹት የፓርቲው የምርጫ የአሰራር ሥርዓት መመሪያ በየደረጃው ለሚገኙ የፓርቲ አባላትና አመራሮች የማስገንዘብና የማስተዋወቅ ተግባራት እስከታችኛው የፓርቲ መዋቅሮች ዘንድ ማድረስ ተጠናክረው መቀጠል አለበት፡፡
ከክልል እስከ የብልፅግና ሕብረት ድረስ በየደረጃው የተገኙ የኢንስፔክሽን ግኝቶች ላይ ግብረ መልስ ለክልልና ከተማ የፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመስጠት መግባባት መድረስ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
በኢንስፔክሽን ቡድኑ በየደረጃው ያለው የምርጫ መመሪያ አፈጻጸም ሁኔታ በአካል በመገኘት ያካሄደው ምልክታ የምርጫ ሂደቱ አገሪቷ የምርጫ ህግ ጋር የተናበበ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሸንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ም/ዋና ኮሚሽነር ያሲን ሐቢብ ናቸው፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ዋና ፀሀፊና የዋና ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ በበኩላቸው የብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን የምርጫ አሰራር ስርዓት ላይ የተካሄደው የኢንስፔክሽን የአሠራር ስርዓት ተፈጻሚነት የጎላ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡
አክለውም የፓርቲ የምርጫ አሰራር ስርዓት የተስተዋሉ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እና በጉድለት የተለዩትን የእቅድ አካል በማድረግ በክልሎች መካከል የተቀራረብ አፈጻጸም ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ኮሚሽኑ በየደረጃው ተለይተው የተሰጡ የግኝቶች ግብረ-መልስ አፈፃፀም ትኩረት በመስጠት ክትትል እንደሚደረግ በግምገማው ማጠቃለያ ተገልጾዋል፡፡
ኮሚሽኑ ለሱፐርቪዥን ቡድኑ አባላት እንዲሁም በየደረጃው ትብብር ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
#Prosperity