የፌዴራል ተቋማት ብልፅግና ወጣቶች ክንፍ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ መርሀግብር በአዲስአበባ ከተማ አካሄደ
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በሚል መሪ ቃል የፌዴራል ተቋማት ብልፅግና ወጣቶች ክንፍ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ መርሀግብር በአዲስአበባ ከተማ አካሂዷል።
በመርሃግብሩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታና የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ም/ፕረዚዳንት ፈዲላ ቢያ፣
የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ም/ፕሬዚዳንት እና የጽ/ቤት ኃላፊ አባንግ ኮሙዳን፣ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የፌደራል ተቋማት ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ገዛኸኝ አንዳርጌ፣ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ሰብለ በቀለ እንዲሁም የክላስተር አስተባባሪዎችና የወጣት ክንፍ አመራሮች እና አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።
በምርጫ ቅስቀሳ መርሀግብር የወጣቶች ክንፍ አመራሮች ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ወጣቶች በብልፅግና ፓርቲ ተጠቃሚነታቸው መረጋገጡና ተሳትፏቸው ማደጉን አውስተው፥ የትውልድ ፓርቲ የሆነው ብልፅግና በቀጣይ ምርጫ አሸናፊ እንዲሆን ወጣቶች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ወጣቶች የሰላም ዘብ በመሆን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የላቀ አስተዋጽኦቸውን እንዲያበረክቱና ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል።