Prosperity Party

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የነበሩበትን ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች ለመፍታት የለውጡ መንግሥት በዘርፉ ያደረገው ሪፎርም በር ከፋች ነበር- ቢኒያም ኤሮ ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ

በኢትዮጵያ የዘመናዊ ሚዲያ ታሪክ ፈር ቀዳጁና የጥንቱ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የነበሩበትን ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች ለመፍታት የለውጡ መንግሥት በዘርፉ ያደረገው ሪፎርም ተቋሙ ዓበይት የለውጥ እመርታዎችን እንዲያሳይ በር ከፋች ነበር ሲሉ አካፍለዋል። መዋቅራዊ ክፍተቶች፣ ግልጽ ያልሆነ ኤዲቶርያል ፖሊሲ፣ የብዝሃነትና ተደራሽነት ፈተና እንዲሁም የቴክኖሎጂ ኋላ ቀርነት ተቋሙን የፈተኑት ማነቆዎች ነበሩ።

ለውጡ እነዚህን ተግዳሮቶች ደረጃ በደረጃ ለይቶ በማረም ስኬቶችን አስመዝግቧል። ከነዚህም መካከል በርከት ያሉ ስቱዲዮዎችን በክልል ከተሞች ማስፋፋት፣ የዲጂታል ሚዲያ ተፎካካሪነትንና ዓለም አቀፍ የሚዲያ አጋርነትን ማጠናከር፣ የሀገርኛ ቋንቋዎችን በመጨመር ተደራሽነትን ማስፋት የሚሉት ከብዙ ጥቂቶቹና ዋነኞቹ ስኬቶች ናቸው።

#PMOEthiopia

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party