የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ንቅናቄ በሁሉም የኦሮሚያ አካባቢዎች እየተካሄደ ነዉ
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ንቅናቄ ወጥነቱን በጠበቀ መልኩ በሁሉም የኦሮሚያ አካባቢዎች እየተካሄደ ነዉ።
በዚሁም መሰረት በአዳማ ከተማ ቦሌ እና ቦኩ ሸነን ክፍለ ከተሞች፣ በምስራቅ ባሌ ጊንዲር ከተማ፣ በቄለም ወለጋ ጅማ ሆሮ ወረዳ እንዲሁም በቢሾፍቱ ከተማ በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች ምርጫ ቅስቀሳ መርሀግብር ተካሂዷል።
ብልፅግና ፓርቲ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ባለፉት አምስት ዓመታት ሰፊ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል። በሚቀጥሉት አምስት ዓመታትም አስተማማኝና ተቋማዊ መሰረት ያለው የፖለቲካ ባህል በመገንባት፤ ዘላቂ ሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ ብሔራዊ መግባባት፣ የዜጎች ክብር፣ ፍትሃዊነት እና የጋራ ብልፅግና የተረጋገጠባትን ሀገር ለመገንባት ይሰራል።
ብልፅግና ፓርቲን ይምረጡ!
የምርጫ ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!
#prosperity