የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል
“ኢትዮጲያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል የተጀመረዉ የብልፅግና ፓርቲ የ"ምረጡኝ" የቅስቀሳ መርሃ-ግብር በምዕራብ አርሲ፣ በምስራቅ ሸዋ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና በቡኖ በደሌ ዞኖች በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።
በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ እና ወረዳ በተካሄደው መርሃ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ጀሚላ ሲምቢሩ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ ፓርቲው ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያን ከጥገኝነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር ረገድ ከፍተኛ ስኬት ማስመዝገቡን ገልጸዋል። በመጪዎቹ አምስት ዓመታትም የሀገሪቱን ብልጽግና በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም ህዝቡ ለብልጽግና ፓርቲ ድምጹን እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።
የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ሀጂ እና የዶዶላ ከተማ ከንቲባ አቶ አዩብ ዱሌ በበኩላቸው ፓርቲው ለትውልድ ዋስትና የሚሆን የልማትና የዲሞክራሲ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በተመሳሳይ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በበቾ ወረዳ ቱሉ ቦሎ ከተማ እንዲሁም በምስራቅ ሸዋ ዞን በዱግዳ ወረዳ እና በመቂ ከተማ የፓርቲው ደጋፊዎችና አባላት በነቂስ በመውጣት ለፓርቲው ያላቸውን አጋርነት አሳይተዋል። ነዋሪዎቹ የዜጎችን መብት የሚያስከብር፣ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥና የሀገርን ሉዓላዊነት የሚያስከብር ፓርቲ በመሆኑ ብልጽግናን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በቡኖ በደሌ ዞን በጮራ ወረዳ በተካሄደ የቅስቀሳ መርሃ-ግብር ላይ የዞኑ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ታቱ ቴሶ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ፓርቲው ኢትዮጵያን ካጋጠማት ዘርፈ ብዙ ቀውሶች ታድጎ ወደ እድገት ጎዳና እየመራት መሆኑን ጠቁመዋል።
ብልፅግናን ይምረጡ!
የምርጫ ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!