የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት በሲዳማ ክልል በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በብላቴ እና በቦሪቻ ወረዳዎች ለአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ያስገነባውን 8 የመኖሪያ ቤቶችን አስረከበ
የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት በሲዳማ ክልል በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በብላቴ እና በቦሪቻ ወረዳዎች ለአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ያስገነባውን 8 የመኖሪያ ቤቶችን አስረከበ።
የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት በሲዳማ ክልል በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በብላቴ እና በቦሪቻ ወረዳዎች ለአቅመ ደካማ አካል ጉዳተኞች ያስገነባውን 8 ዘመናዊ ቤቶችን ከነሙሉ የቤት ቁሳቁስ ለተጠቃሚዎች በዛሬው ዕለት አስረክቧል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እንደገለጹት ብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር ፓርቲ መሆኑን በተግባር እየገለጸ መሆኑን በማንሳት የሰው ህይወት እንዲሻሻል እና እንዲለወጥ በልዩ ትኩረት የሚሰራ ፓርቲ ብልፅግና መሆኑን አንስተዋል።
አቶ አብርሃም አክለው እንደገለጹት ብልፅግና ፓርቲ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች በእኩልነት የሚያገለግል ሰው ተኮር ፓርቲ ነው በማለት ብልፅግና ስርዓት እና ሰው ያበላሽውን ለማረም እና ለማስተካከል እየተጋ የሚገኝ ፓርቲ ነው በማለት ብልፅግናን በማስቀጠል ድህነትን ታሪክ ለማድረግ በትጋት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የሀብት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ፈይሳ በበኩላቸው መልካም ስራን ለማስቀጠል ብልፅግና ፓርቲ ለሰዎች ኑሮ መሻሻል የሚተጋ ፓርቲ ነው በመሆኑ ዛሬ ሲዳማ ላይ የተገነቡ ቤቶች ከእሴቶቻችን መካከል የሆነውን መረዳዳትን መሰረት አድርገን የተገነቡ የአቅመ ደካማ ቤቶች መሆናቸውን በማንሳት ብልፅግና ፓርቲ የማህበረሰባችንን እሴት የሆኑትን መረዳዳትን ፣ መተሳሰብን እና አብሮነት ይበልጥ ጎልብተው እንዲቀጥሉ መላው አባላት እና ደጋፊዎች በትብብር መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።
የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ፃዲቁ በጢሶ በበኩላቸው በመርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ብልፅግና የበርካቶችን እንባ በማበስ ታሪክ እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው በማለት የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት በዞኑ በመገኘት ላደረገው አስተዋጽኦ ትልቅ ምስጋና እንዳላቸው በመግለጽ ይህ አይነት አቅመ ደካማ ዜጎችን በተለይም በህዝቦች መካከል የኖረውን የመደጋገፍ ባህልን እንደሚያጠናክር የገለፁት ኃላፊው እንደ ዞን ይህን መሠል ስራዎች ለማስቀጠል እንደሚሰራም ገልፀዋል ።
በመርሐ ግብሩ ላይ የፌደራል እና የክልል አመራሮች በተገኙበት ዘመናዊ ቤቶችን ከነሙሉ የቤት ቁሳቁስ ለተጠቃሚዎች ርክክብ ተካሂዷል።
#prosperity