Prosperity Party

የብልፅግና ፓርቲ በዜጎች መካከል እውነተኛ ወንድማማችነትንና እህታማማችነትን በማሳደግ ጠንካራና ቅቡልነት ያለዉ ሀገር ሀገረ መንግሥትና የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ኢትዮጵያን ለመገንባት በትኩረት እየሰራ ይገኛል” — መንግስቱ በቀለ (ዶ/ር)

የብልፅግና ፓርቲ በአሰላ ከተማ እያካሄደ ባለው የ"ምረጡኝ" ቅስቀሳ መርሀግብር ላይ የአርሲ ዞንና የአሰላ ከተማ ነዋሪዎች ሆብለዉ በመዉጣት ለፓርቲው ያላቸውን ድጋፍ እያሳዩ ነው።

በኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የጽህፈት ቤት የድርጅት ዘርፍ ኃላፊ መንግስቱ በቀለ ዶ/ር ባስተላለፉት መልዕክት ብልፅግና ፓርቲ ለሀገር ግንባታ ምሰሶ የሆኑ ትክክለኛ እይታዎችንና አስተሳሰቦችን አንግቦ በመደመር መንገድ ጉዞ መጀመሩን ገልጸዋል። ለግጭት መንስኤና ለልዩነት ምንጭ በመሆን የዜጎችን አብሮ የመኖርና የወንድማማችነት እሴት ሲፈትኑ የነበሩ የተሳሳቱ ከፋፋይ ትርክቶችን በወል ትርክት በመተካት፣ በዜጎች መካከል እውነተኛ ፍቅርንና ወንድማማችነትን በማሳደግ፣ ብዝሃነት ያላት፣ ጠንካራና ቅቡልነት ያለዉ ሀገር መንግሥት ለመገንባት እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ብልፅግና ፓርቲ ለህዝቦች ታሪክና ባህል ትልቅ ቦታ እንደሚሰጥና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰራም ገልጸዋል። የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከወደቀበት በማንሳት እንዲያገግም ያደረገው የብልፅግና ፓርቲ፣ ዛሬም በሁሉም ዘርፎች በትኩረት እየተሰሩ ባሉ ስራዎች የማህበረሰባችንን ችግሮች የሚፈቱና የሀገርን ኢኮኖሚ የሚደግፉ ስኬቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ጠቅሰው፣ በዚህም የኢትዮጵያ ተሰሚነት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲጨምር ሆኗል ብለዋል።
በመጨረሻም ብልፅግና ፓርቲ ቃሉን በተግባር መፈጸምን ባህል ያደረገ ፓርቲ መሆኑን ባለፉት አምስት ዓመታት አፈጻጸሙ ያረጋገጠ መሆኑንና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ለማሸጋገር በአዲስ ቃል ኪዳን የቀረበ መሆኑን አንስተዋል። ለሀገራችንን ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ይዞ ለቀረበው የብፅግና ፓርቲ ድምፃችሁን ስጡ ብለዋል።
ብልፅግናን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!
ወደ ተምሳሌት ሀገር ከብልፅግና ጋር!

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party