የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች በድምቀት ቀጥሏል
የብልጽግና ፓርቲ 7ኛውን አገራዊ ምርጫ መነሻ በማድረግ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" በሚል መሪ ቃል በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች እያካሄደ ያለው የምርጫ ቅስቀሳ በከፍተኛ መነሳሳት ቀጥሎ ውሏል።
በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ በምስራቅ ቦረና ዞን አሬሮ ወረዳ፣ በቄለም ወለጋ ዳሌ ዋበራ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሰደን ሶዶ፣ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ጂማ ገነት እና አባቦ ጉድሩ ወረዳዎች የፓርቲው ደጋፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ደማቅ የቅስቀሳ መርሃ ግብሮች ተካሂደዋል።
በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ በተካሄደው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነመራ ቡሊ ብልጽግና ፓርቲ ከትላንት ድሎች ይልቅ የነገውን ታላቅ ህልም ለማሳካት በቆራጥነት እየሰራ ሲሆን፣ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር በገባው አዲስ ቃል ኪዳን ጉዞውን አጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል:: በብልፅግና እሳቤ በተፈጠረዉ ሚዛናዊ እና አካታች የፖለቲካ ምህዳር የኦሮሞ ሕዝብም ተጠቃሚ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አክለዉም የጥልቻ ምዕራፍ ተዘግቶ የይቅርታ፣ የፍቅርና የአንድነት ድልድይ በመገንባት፣ ኢትዮጵያ በሁሉም ረገድ በጽኑ መሰረት ላይ እንድትቆም ፓርቲው እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
አቶ ነመራ፣ፓርቲው ባለፉት አምስት ዓመታት ያስመዘገባቸውን ውጤቶች እንደ ስንቅ በመጠቀም፣ ኢትዮጵያን የአፍሪካና የዓለም የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
ታዳሚ ደጋፊዎቹም ባስተላለፉት መልዕክት፤ "በሕዝብ ትግል የመጣውንና የሕዝብን ችግር በጥናት ላይ ተመስርቶ እየፈታ ያለውን የብልጽግና ፓርቲን ለመምረጥ ዝግጁ ነን" በማለት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
በተመሳሳይም በኢሉ አባ ቦር ዞን ዲዱ ወረዳ እና በምስራቅ ወለጋ ሲቡ ሲሬ ወረዳዎች የቅስቀሳ ንቅናቄው የቀጠለ ሲሆን፣ ፓርቲው የለውጡን ጉዞ በማስቀጠል የነገዋን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል።
ብልጽግናን ይምረጡ!
የምርጫ ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!