የብልጽግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ በመታሃራና ፈንታሌ በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ
"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" በሚል መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ በምሥራቅ ሸዋ ዞን፣ መታሃራ ከተማና ፈንታሌ ወረዳ ለ7ኛው አገር አቀፍ ምርጫ የሚያደርገውን የቅስቀሳ መርሃ-ግብር በታላቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ አካሂዷል። በዕለቱ የተገኙ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ፓርቲው ያስመዘገባቸውን ስኬቶችና ለቀጣይ አምስት ዓመታት የያዛቸውን ግዙፍ ዕቅዶች ለሕዝቡ አብራርተዋል።
የኦሮሚያ ጨፌ ምክትል አፈ-ጉባኤ አቶ ኤልያስ ኡመታ በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያን በሁሉም መስክ የምትመች አገር ለማድረግ ሲሠራ መቆየቱን ገልጸዋል። አቶ ኤልያስ አያይዘውም ፓርቲው የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በገባው ቃል መሠረት የዲሞክራሲ ሥርዓትን በመገንባት፣ ሁሉንም ዜጋ ያሳተፈ የልማት ጉዞን በማስቀጠል ረገድ ተጨባጭ ውጤቶችን እያመጣ መሆኑን አስገንዝበዋል። ፓርቲው ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡትን የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ድሎችን ይበልጥ በማጠናከር አገሪቱን ወደ ላቀ የብልጽግና ምዕራፍ እንደሚያሸጋግራትም በጽኑ ቃል ገብተዋል።
በተመሳሳይ መልኩ የምሥራቅ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባቡ ዋቆ ብልጽግና ፓርቲ በተለይም በዞኑ ውስጥ የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ያከናወናቸውን ተግባራት አድንቀዋል።
ብልጽግና ፓርቲ በተግባር የሚመራ ፓርቲ መሆኑን ባለፉት ዓመታት በተከናወኑት እንደ ስንዴ ኤክስፖርት፣ የአረንጓዴ አሻራ እና ግዙፍ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች አሳይቷል፣" ያሉት አቶ አባቡ፣ ፓርቲው በፈተናዎች ውስጥ አልፎ የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ዳር ማድረሱ ለቀጣይ ድል ትልቅ ዋስትና መሆኑን ገልጸዋል።
አስተዳዳሪው አክለውም፣ ዞኑ ለፓርቲው ስኬት ትልቅ ድርሻ እንዳለውና ሕዝቡም የጀመራቸውን የልማት ሥራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል ለብልጽግና ፓርቲ ድምፁን እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል። በዕለቱ የተገኘው የኅብረተሰብ ክፍልም ለፓርቲው ያለውን ድጋፍ በታላቅ ድምቀት የገለጸ ሲሆን፣ ምርጫው በሰላምና በዲሞክራሲያዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን እንደሚወጣ አረጋግጧል።
ብልፅግናን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!
#prosperity