የሸዋሊድ በዓል የአብሮነትና የመቻቻል እሴቶችን ይበልጥ ማጎልበት በሚያስችል መልኩ-እየተከበረ ነው-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ
የሸዋሊድ በዓል ሀረር የምትታወቅባቸውን የአብሮነትና የመቻቻል እሴቶችን ይበልጥ ማጎልበት በሚያስችል መልኩ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ እንደሚገኝ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
የሹዋሊድ በዓል በሀረር ከተማ በተለያዩ መርኃ ግብሮች በመከበር ላይ ይገኛል፡፡
በበዓሉ ላይ በርካታ ሴቶችና ወጣቶች በባህላዊ አልባሳት ደምቀው ባህላዊ ጭፈራዎችን እና ዜማዎችን እያሰሙ ይገኛሉ።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት በዓሉ ሀረር የምትታወቅባቸውን የአብሮነትና የመቻቻል እሴትቶን ይበልጥ ማጎልበት በሚያስችል መልኩ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ የማኅበራዊ እሴቶቻችንን በማጎልበት አንድነት ይበልጥ እንዲጎለብት ከማስቻሉም ባሻገር በክልሉ ያሉ የቱሪዝም ፀጋዎችን በማስተዋወቅ የብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው።
በቀጣይም ባህላዊ ቅርሶቻችንና ሌሎች ድልብ ማኅበራዊ ሀብቶቻችን ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉና ለሀገራችን ተገቢውን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዲሰጡ ይበልጥ አበክረን እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል።
የዘንድሮው በዓል አለም አቀፉን የጁገል ቅርስ ኮሪደር መልሶ ልማት ሙሉ በሙሉ በተጠናቀቀበት ማግስት መከበሩ ልዩ እንደሚያደርገውም ገልፀዋል።
በክብረ በዓሉ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣የቱሪዝም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሰላማዊት ካሳ፣ የክልሉ የመንግስትና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች፣የክልሉ ነዋሪዎችና ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍል በበአሉ ለመታደም የተገኙ እንግዶች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።
የሹዋሊድ በዓል በዩኔስኮ ከማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል መመዝገቡ ይታወሳል።