Prosperity Party

የሴቶችን የአመራርነትና የውሳኔ ሰጪነት ተሳትፎን ለማሳደግ የሁላችንንም ርብርብ የሚጠይቅ ነው- ወ/ሮ ዘሃራ ዑመድ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ፕሬዝዳንት

ሰላም ሚኒስቴር ከሴቶች አደረጃጀት ጋር በመተባበር "በሴቶች ተሳትፎ የጸናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሃሳብ ሀገራዊ የንቅናቄ ማጠቃለያ መድረክ አካሂዷል። 

የብልጽግና ሴቶች ክንፍ ፕሬዘዳንት ወ/ሮ ዘሃራ ዑመድ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ በአመራርና በውሳኔ ሰጪነት ተሳትፏቸው ወደፊት እንዲመጡ ለማስቻል እና በቂ ውክልና እንዲኖራቸው ለማድረግ የሁላችንን ርብርብ የሚጠይቅ ነው፡፡

ባለፉት ዓመታት ሴቶች በአገራችን አካታችና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲሁም የመንግስት ኢንሼቲቮችን በንቀናቄ በመምራት ከፍተኛ አስዋጾኦ ሲያበረክቱ መቆይታቸውን አስታውሰዋል፡፡ 

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ በሆነ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የአገራችን ሴቶች የእጩነትም ሆነ የመራጭነት ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

እንደ ሀገር ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ሴቶች ዋና ተዋናይ በመሆን በቀዳሚነትና በመሪነት ማህበረሰባዊ ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ታሳቢ ያደረገ የንቅናቄ መድረኮች ከቀበሌ ጀምሮ  በሁሉም ክልሎች በተለያዩ ኩነቶች ታጅቦ ለአንድ ወር ያህል ሲካሄድ መቆየቱን ጠቅሰዋል፡፡ 

የሰላም ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው በአገራችን ሁለንተናዊ ሰላም ለማረጋገጥ የጠንካራ ተቋማትና የማኅበረሰብ ትስስርና ተሳተፎ ወሳኝ ነው፤ በዚህም ረገድ የሴቶች አበርክቶ ከፍተኛ በመሆኑን ገልጸዋል፡፡   

ሴቶች ሰላምን ለማረጋገጥ ራሳቸው በሚያረክቱት ተግባር ብቻ ሳይሆን የሰላም አርበኞችን በመፍጠር ጉልህ ድርሻ እየተወጡ ይገኛል ብለዋል፡፡  

ሰላምን ለማጽናት ከተለያዩ የሴቶች እንዲሁም የወጣት አደረጃጀቶች ጋር  በመሆን እየሰሩ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡ በምርጫ ወቅት በየአካባቢው በሚደረጉ ቅሰቀሳዎች ያልተፈለጉ ሁከቶች እንዳይከሰቱ ሴቶች የሰላም አምባሳደር  እንዲሆኑም አሳስበዋል፡፡ 

ባለፉት የለውጥ አመታት ሴቶች በፓለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ተጠቃሚነታቸው ማረጋገጥ መቻሉን የገለጹት ደግሞ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

በኢኮኖሚው ዘርፍ ሴቶች የሃብት ባለቤት እንዲሆኑ የተከናወኑ ተግባራት ታሪካዊ ለውጥ አምጥተዋል ብለዋል፡፡ 

በ7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ሴቶች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የመንግስት ስልጣን ምንጭ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንዲሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party