Prosperity Party

የሀገራችንን ተጨባጭ የህዝቦችን ጥያቄዎችን እየመለሰ የሚገኘው ብልፅግና ፓርቲ ነው:- አቶ ደስታ ሌዳሞ

የሀገራችንን ተጨባጭ የህዝቦችን ጥያቄዎችን እየመለሰ የሚገኘው ብልፅግና ፓርቲ ነው:- አቶ ደስታ ሌዳሞ

በሲዳማ ክልል የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ በመገኘት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንደገለጹት ምርጫ የዴሞክራሲያዊነት መገለጫ በመሆኑ መጪው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ፣ ፍትሃዊ እና በህዝቦች ዘንድ ቅቡልነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ እንደ ክልል እንደሚሰራ በማንሳት ብልፅግና ፓርቲ እንደ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ምርጫውን ለማሸነፍ እንደሚሰራም አንስተዋል።

ብልፅግና ፓርቲ የሀገራችንን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ውስብስብ ችግሮች እና ጥያቄዎችን እየፈታ የሚገኝ ጠንካራ ፓርቲ ነው በማለት ሀገራችንን ተምሳሌታዊ ሀገር ለማድረግ እና የህዝባችንን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ በቀጣይነት በትጋት እንደሚሰራ በመግለጽ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሕዝባችን ቃል የምንገባው፣ ከተመረጥን ያለምነውን ሁለንተናዊ ብልፅግና ሌት ተቀን በመሥራት ያለምንም መሸራረፍ እንፈጽማለን በማለት ተናግረዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በበኩላቸው ፓርቲው ሀገር በቀል በሆነው "የመደመር" እሳቤ በመመራት በቃሉ ታምኖ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች በርካታ መሆናቸውን አንስተዋል።

የብልፅግና ምርጫ ምልክት" የስንዴ ነዶ" ነው በማለት የስንዴ ነዶ የመደመር ፣ የአንድነት እና የትብብር ተምሳሌት ነው መሆኑን በማንሳት ሀገራችንን የጀመረቸውን የብልፅግና ጉዞ ለማሳካት በትብብር እና በአንድነት መቆም ይገባናል ብለዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅ/ፅ/ቤት የ7ኛው ሀገራዊና ክልል አቀፍ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቅያ ፕሮግራም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም የፓርቲያችን አባላት እና ልዩ ልዩ የህብረሰብ ክፍሎች በተገኙበት ተካሂዷል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party