Prosperity Party

የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ በሀረር ከተማ ታላቅ የምረጡኝ ቅስቀሳ እያካሄዱ ነው

የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ «የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና እኩልነት በብልፅግና ፓርቲ ይረጋገጣል!» በሚል መሪ ቃል፣ በታሪካዊቷ የሀረር ከተማ 7ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ ደማቅ የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሂዷል።

በዕለቱ የፓርቲው ሴቶች ክንፍ አመራሮች፣ አባላትና በርካታ ቁጥር ያላቸው የከተማ እና የገጠር ሴቶች በተገኙበት በተካሄደው በዚህ የቅስቀሳ መድረክ ላይ፤ ብልፅግና ፓርቲ ለሴቶች የሰጠውን የላቀ ስፍራና በቀጣይ ይዞራቸው የተነሳቸውን ግልጽና አታጋይ እቅዶች ይፋ አድርጓል።
ብልፅግና ፓርቲ ሴቶችን የሀገር ግንባታና የብልፅግና ጉዞ ዋና ምሰሶ አድርጎ እንደሚመለከት የገለጹት የክንፉ አመራሮች፤ በቀጣዩ የምርጫ ዘመን ሴቶችን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሶስት ዋና ዋና ምሰሶዎችን አንስተዋል፦
ሴቶች በፖለቲካው መድረክ ያላቸው ተሳትፎ የማስጌጫ ሳይሆን የውሳኔ ሰጪነት እንዲሆን ፓርቲው በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።
በክልልም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሴቶች ወደ አመራርነት እንዲመጡና ድምፃቸው የፖሊሲዎች መቅረጫ እንዲሆን ብልፅግና ብቸኛውና አስተማማኙ አማራጭ ነው ብለዋል።
የሴቶችን ጤና ማረጋገጥ፣ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ተደራሽ ማድረግና በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ማናቸውንም አይነት ጥቃቶች መከላከል የፓርቲው ቀዳሚ ማህበራዊ እሳቤዎች ናቸው።
ሴቶችን የኢኮኖሚው ጥገኞች ሳይሆን የሀብት ፈጣሪዎችና ባለቤቶች ማድረግ። ይህንን ለማረጋገጥም አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞችን ማስፋፋት፣ የብድርና የቴክኖሎጂ አቅርቦቶችን ማመቻቸት እንዲሁም ሴት አምራቾችን ማበረታታት ዋነኛ የብልፅግና ስትራቴጂ ነው።
የሴቶች ብልፅግና ሳይረጋገጥ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና ሊታሰብ አይችልም። ፓርቲያችን ብልፅግና በተግባር ያሳየውን የሪፎርም ስራ አጠናክሮ በመቀጠል፣ ሴቶች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ እኩል ተጠቃሚና ባለቤት የሚሆኑባትን ኢትዮጵያ ለመገንባት ቃል ገብቷል።
የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ የከተማዋ ሴቶችና መላው ህዝብ በቀጣዩ 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ፣ የተጀመረውን የለውጥና የብልፅግና ጉዞ ለማስቀጠል የምልክታችን የሆነውን ስንዴ ነዶ በመምረጥ ድምፃቸውን ለብልፅግና ፓርቲ እንዲሰጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party