ክልላዊ የሴቶች የድጋፍ ሰልፍና የሴት እጩዎች ትውውቅን በማስመልከት የተዘጋጀ የእግር ጉዞ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሄደ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሴቶች ክንፍ 7ተኛው ዙር ሀገራዊና ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫን በማስመልከት ክልላዊ የሴቶች የድጋፍ ሰልፍና የሴት እጩዎች ትውውቅ መርሃ-ግብር አካሂዷል፡፡
በመርሃ-ግብሩ ክልላዊ የሴቶች የድጋፍ ሰልፍና የሴት እጩዎች ትውውቅን በማስመልከት የተዘጋጀ የእግር ጉዞ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በፕሮግራሙ በ 7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ብልፅግና ፓርቲን በመወከል ለክልልና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረቡ ዕጩዎች ትዉዉቅ የሚካሄድ ይሆናል።
በድጋፍ ሰልፉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል ጫላን ጨምሮ የቅ/ጽ/ቤቱ አመራሮች፣ የብልፅግና ፓርቲ የሴት ዕጩዎች፣ የወላይታ ዞንና ሶዶ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች፣ የብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በመሳተፍ ላይ ናቸዉ።