Prosperity Party

ኢትዮጵያ እየተከለች ነው!

ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ቃል ዛሬ በመላው አገሪቱ ታላቅ ህዝባዊ ንቅናቄ እየተካሄደ ይገኛል። በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የታቀደው ታሪካዊ መርሃግብር ከንጋት ጀምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ብርድና ዉርጭ፣ ዝናብና ጭቃ ሳይበግራቸዉ ያለ ልዩነት ከማለዳው ጀምረው በየአካባቢያቸው የተለያዩ ችግኞችን በመትከል አሻራቸውን ለትዉልድ እያኖሩ ነው። 

በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል እየተከናወነ ያለው ታላቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ፣ የመደመር እሳቤ በተግባር የተገለጠበት ህያው ማሳያ ነው።

 ይህ ሃገራዊ መርሃግብር ትውልድ እና አገርን የማሻገር፣ የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያ በጽኑ መሰረት ላይ የመገንባት ታላቅ አገራዊ ሀላፊነት ነዉ።

 የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በመደመር መንግስት ፊት አዉራሪነት  ሀገር በቀል እውቀት እና የራስ እምቅ አቅም በመጠቀም ፀጋዎቻችን በመንከባከብና የሰው ሀይል አስተባብሮ የነገን ብሩህ ተስፋ በራስ አቅም መገንባት እንደሚቻል በተግባር ያረጋገጠ ስኬታማ ተግባር ነዉ።

ዛሬ ሁላችንም የምንተክለው እያንዳንዱ ችግኝ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና የምናበረክተው አሻራ ስለ ሆነ ዛሬውኑ በተከላ ቦታዎች በመገኘት ተስፋን እንትከል፣ ኢትዮጵያን አርንጓዴ እናልብሳት ፣የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ በተግባር እናረጋግጥ!

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party