Prosperity Party

አራተኛዉ የ'ኢትዮጵያ ታምርት' ኤክስፖ 2018 ኤክስፖ ተከፈተ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን የአምራች ዘርፍ ለማስፋፋት የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክረውን አራተኛውን 'ኢትዮጵያ ታምርት' ኤክስፖ 2018 ዛሬ በይፋ መርቀው ከፍተዋል።

‎‎ኤክስፖው  እስካሁን  ያሳያቸው እና የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች፦

‎- የአምራች ዘርፉ ግብዓት አቅርቦት በዓመት 9 ሚሊዮን ወደ 15 ሚሊዮን ቶን አድጓል፤

‎- ለአዳዲስ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶች 3.4 ጊጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ቀርቧል፤

‎- ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርበው የፋይናንስ አቅርቦት 8.1 ቢሊዮን ወደ 50 ቢሊዮን ብር ያደገ ሲሆን ለከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ደግሞ 262 ቢሊዮን ብር በላይ ከፍ ብሏል፤

‎- ለዘርፉ 2.28 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ተመድቧል፤

‎- የፋብሪካዎች የማምረት አቅም 47 በመቶ ወደ 67 በመቶ አድጓል፤

‎- የማምረት አቅምና ዕድገት 4.8 በመቶ ወደ 10.7 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን፣ በቀጣይም ተጨማሪ ዕድገት ይጠበቃል፤

‎- ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት እስከ 4.85 ቢሊዮን ዶላር ማዳን የተቻለ ሲሆን የወጪ ንግድም ከፍተኛ እድገት እያሳየ ይገኛል፤

‎- 2,800 በላይ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ የተቻለ ሲሆን፣ 1.4 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።

‎‎ኤክስፖው ኢንዱስትሪዎችን የሚያስተሳስር፣ ኢንቨስትመንትን የሚስብ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ አምራቾችንና በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎችን የሚያገናኝ ቁልፍ ሀገራዊ መድረክ ሆኗል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party