ተስፋን እንትከል
"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል ።
በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሣሽነት "የአረንጓዴ ዐሻራ" መርሐ ግብር ሲጀመር፣ ዓላማው የኢትዮጵያን የደን ሽፋን ማሳደግ፣ የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል እና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንዲሁም አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት እየተከናወነ ያለ ታላቅ ሀገራዊ ንቅናቄ ነው።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአየር ንብረት ተፅዕኖዎችን ለመቋቋም ኢትዮጵያ ከሰጠቻቸው በራስ አቅም የተመሰረቱ ምላሾች አንዱና ዋነኛው ተግባር
ነው ።
አረንጓዴ አሻራ የአገራችንን አካባቢ ለመጠበቅ፣ የደን ሽፋንን ለማሳደግ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ፣በምግብ እራስን ለመቻል እና ለቀጣይ ትውልድ አረንጓዴ አካባቢን ለማስረከብ የሚካሄድ ግዙፍ ሀገራዊ እንቅስቃሴ ጭምርም ነው።
ችግኝ መትከል ዛሬን ከማስዋብ በላይ የነገን ህይወት መጠበቅ ስለሆነ ሁላችንም በመርሃ ግብሩ በንቃት በመሳተፍ አረንጓዴ፣ ውብ እና ለኑሮ ምቹ አካባቢ መፍጠር የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት እንደሆነ ይታወቃል ።
ሀምሌ 27/2018 ዓ/ም በዛሬው እለት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የዓለምን ክብረ ወሰን በድጋሚ ለመስበር ሁላችንም በነቂስ በመውጣት እየተከልን እንገኛለን ።
ባለፉት የዘመቻ ዓመታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ከዳር እስከ ዳር በመንቀሳቀስ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን ተክለዋል።
ይህ መርሐ ግብር ተመናምኖ የነበረውን የደን ሽፋን እንዲታደስ ከማድረግ ባለፈ የአየር ንብረት ለውጥንና
የምግብ ዋስትናን እንደሚያረጋግጥ ተስፋ ተጥሎበት እየተተገበረ ያለ ታላቅ ሀገራዊ ንቅናቄ ነው።
የኢትዮጵያ የደን ሽፋን መርሐ ግብሩ በ2011 ዓ.ም ሲጀመር ከነበረበት 17 ነጥብ 2 በመቶ አሁን ላይ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ያደገ ሲሆን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ተጠናክሮ መቀጠል የደን ሽፋንን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ።
በአጠቃላይ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለ ሀገርን ለማስረከብ ያለመ ተግባር ነው።