ብልፅግና ፓርቲ የ9 ወራት የዕቅድ ሥራ አፈጻጸሙ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ
የብልፅግና ፓርቲ የ9ወራት የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በዛሬው እለት ተካሂዷል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የፓርቲያችን የ9 ወራት የዕቅድ ሥራ አፈጻጸም በጥልቀት ተገምግሟል፡፡
በመርሀ ግብሩ ፓርቲያችን ለመድረስ ያስቀመጣቸውን የዕሳቤ፣ የዕቅድ፣ የተግባር እና የውጤታማነት ደረጃዎች በጥልቀት ተፈትሿል፡፡
በዚህ መሠረት ፓርቲው በዕቅድ የያያዛቸው ሥራዎች በዕቅዱ መሰረት እና ከዛ በላይ መፈጸሙን ገምግሟል፡፡
የፓርቲው የመፈጸም አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ፤ ለህዝብ የገባውን ቃል በተግባራዊ ውጤት ማረጋገጥ መቀጠሉን፣ ተቋማዊ ስታንዳርዳይዜሽን መገንባቱን እንዲሁም በቀጣይነት የተለማቸውን ትልሞች በላቀ የአመራር ብቃት፣ ተቋማዊ አቅም እና ተነሳሽነት እየፈጸመ ለመቀጠል ያለዉን የምልዓተ አመራሩ እና የአባላቱ ዝግጁነት አረጋግጧል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ከመደበኛ ሥራዎች ጎንለጎን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃና ፍትሓዊ እንዲሆን የተጀመሩ ሥራዎችን በውጤታማነት ከማስቀጠል አንፃር መላው የፓርቲያችን አደረጃጀቶች፣ አመራሮችና አባላት በቁርጠኝነት እንዲንቀሳቀሱ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡